የመጠፋፋት ፓለቲካ

እንደ አለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያ ፓለቲካ መጠፋፋትን ዋና መገለጫው ያደረገ ይመስላል፡፡ በፓለቲካው ዓለም ያለመግባባት የተለመደና ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በሁሉም ጉዳይ ላይ መስማማት ብንችል እንኳ ፈፅሞ ለውጥ ይናፍቀናል እንጅ ቅንጣት ታክል ካለንበት የአስተሳሰብ ደረጃ ከፍ አንልም፡፡ የሀሳብ ልዩነት ለአንድ ማህበረሰብ እርግማን ሳይሆን የለውጥ ነዳጅ ነው፡፡ ከርዕዮተ ዓለም አኳያም ስናየው ልዩነት እጅጉን የላቀ ጠቀሜታ አለው፡፡
ይህ በእንድህ እንዳለ ወደ አገራችን የፓለቲካ ደዌ ስንመለስ•••የኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ልምድ እንደሚያሳየው ልዩነትን የሚሸከም አስተዳደራዊ ትከሻ የለም፡፡ ከገዥው መንግስት አስተምህሮ እና ርዕዮተ ዓለም በተቃራኒው የቆመ ሁሉ ጠላት ነው፡፡ ለነሱ ልዩነቱ ያጠፋናል ብለው ስለሚያስቡት የሀሳቡ ባለቤት መጥፋት አለበት፡፡ በቃ! አጥፍቶ መጥፋት የፓለቲካ መንገድ ይህ ነው፡ መቻቻል የሚባል ነገር ከቶ አይታሰብም፡፡ ይህ አይነት የፓለቲካ አካሄድ ግን በአንድ ጭንቅላት የሚያሰብ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረግ የአላዋቂዎች ሙከራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የፓለቲካ ልዩነቶችን ለማጥፋት መሞከር አገርን የሀሳብ ድህነት ውስጥ ይከታል፤ አማራጭም ያሳጣል፡፡ ግለሰቦች አድራጊ ፈጣሪ ሲሆኑ ከስርዓት ይልቅ ስሜት ሁሉን መምራት ይጀምራል፡፡ በስሜት የሚመራ ፓለቲካ ደግሞ አገርን የዜጎች እስር ቤት ማድረጉ ግልፅ ነው፡፡
የጥላቻ ፓለቲካ መጨረሻው ህዝብን እርስበርስ ማጫረስ ነው፡፡ አጥፍተን እንጠፋለን እንጅ ሌላ ትርፍ የለውም፡፡ ስለዚህ ከጥላቻው የፓለቲካ ጫዎታ ለመውጣት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል፡፡



Comments